Features

Amharic and Geez Made Easy, With New Software ዓማርኛና ግዕዝ በቀላሉ ለመክተብ፣ ግዕዝኤዲት 2.11

Enjoy the following GeezEdit features:

Amharic ዓማርኛ

የግዕዝኤዲት ጥቅሞች፦

 • ኣከታተቡ የተመሰረተው ሳይንስን በመመርኰዝ ነው።  ምሳሌ፦ ዓማርኛ በብዛት የሚጠቀምባቸው ሳድሳን ፊደላት እያንዳንዳቸው በኣንድ መርገጫ ብቻ ይከተባሉ።
 • እያንዳንዱ ቅርጽ ወይም ቀለም ልክ እንደ እንግሊዝኛው በኣንድ መርገጫ ከመከተብ የተረፈው የሚከተበው ከሁለት መርገጫዎች ባልበለጡ ነው።
 • እያንዳንዱ የኮምፕዩተር መርገጫ ወይም ቁልፍ የግዕዝ ስም ኣለው። ኮምፕዩተር ላይ AእስከZያሉት 26 የላቲን ካፒታል ፊደላት የሃያ ስድስቱ የእንግሊዝኛ የኮምፕዩተር የመርገጫ ቍልፎች ስሞች ናቸው። በእዚሁ ዓይነት 37 የኮምፕዩተር መርገጫዎች የሠላሳ ሰባቱ የግዕዝ የመርገጫዎች ስሞች ናቸው። ሠላሳ ሰባት የመርገጫዎች ቊልፎች ለኮምፕዩተር ሲሠሩ ለግዕዝ ቤት የግዕዝ ፊደላት ተስተካክለው ተገኝተዋል። የተረፉትን 10 መርገጫዎች ለኣረቡና ግዕዝ ኣኃዛት ተመድበዋል።
 • ለቁልፎቹ ኣመዳደብ የተጠቃሚው ብዛትና ሆህያት ኣጠቃቀም ተገምተዋል። የተሠራውም ከ፳ ዓመታት በላይ ልምድ ባለውና ግዕዝን በኮምፕዩተር ካቀረቡት ነው።
 • ሥራው የተመረኰዘው ቊጥሩ ሚሊዮን ፱፻፶፯ የሆነ (9,000,957) የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንትና የባለቤትነት መብቱ ሊሰጥ እየተጠበቀ ባለበት (ፔንዲንግ ፓተንት) ኣዲስ ግኝት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በፊደላት ኣከታተብ ወግ ልክ እንደ እንግሊዝኛው በኣንድ መርገጫ ኣንድ የግዕዝ ዩኒኮድ ቀለም እንዲከተብ ተደርጓል። በሁለት መርገጫዎች ቀለም እንደሚደገምና ማንኛውም ቀለም በሁለት መርገጫዎች የሚከተብበት ዘዴ ተፈጥሯል። (ስለዚህ ከኣሁን ወዲያ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች መክተብ በማይችሉ መክተብ ኣያስፈልግም። ከእዚህ በፊት ሲደረግ እንደነበረው ኣንድን ፊደል ለመድገም ሌሎች ሦስት ቀለሞችን ማሳለፍ ወይም ሶስት መርገጫዎችን መጠቀም ወይም ባዶ ስፍራን ቃላት መካከል መተውና ሲያስፈልግም በቀስትና የመሰረዣ መርገጫዎች መሰረዝ ወይም በእንግሊዝኛ ፊደል ከትቦ የስፍራ መርገጫ ሲረገጥ ዓማርኛው እንዲታይ ማድረግ ወይም በማውስ ቃላትን መምረጥ ወይም ቀለሞችን በመጠቆም መክተብ ወይም ዓማርኛውን እስከ ስምንት መርገጫዎችን መጠቀም በሚያስፈልጉ የማያዛልቁ ኣከታተቦች ከማዝገም ተገላግለናል።)
 • የኣቀራረብ ገጽታው ብዙ ሺህ ተጠቃሚዎች ከሚያውቋቸው ሞዴት፣ ኢትዮወርድ እና የመሳሰሉት ፕሮግራሞቻችን ጋር የቀረበ ነው። በዩኒኮድ ፊደል የሚጠቀም ማንኛውም ፕሮግራም ውስጥ በቢለን፣ ቤንች፣ ምኢን፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ዓማርኛ፣ ኦሮሚፋ፣ ጉራጌ፣ ግዕዝና ሌሎች ቋንቋዎች በግዕዝ ሆህያት፣ ኣኃዛት፣ የዜማና ሌሎች ምልክቶች ቀለሞች ያስጽፋል። የግዕዝኤዲት ኣከታተብ በቅርቡ ዩኒኮድ ውስጥ የገቡትን ባስኬቶ፣ ዳውሮና ጉሙዝና ጋሞ ጎፋ ቢያጠቃልልም ገና መደበኛ ስፍራዎቻቸው ላይ ኣልገቡም። ምኢን የፊደል ገበታን የሙርሲ፣ ሱሪ፣ ሳሆ፣ ዲዚና ኦሮሚፋ ቀለሞች ይጋሩታል። ከግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎቻችን ሃዲያ፣ ሓረሪ፣ ሲዳሞ፣ ከምባታ፣ ጌዴዎና ወላይታ ይገኙበታል።
 • ይህ ግዕዝኤዲት / ግእዝኤዲት በእዚህ ኣዲስ የፊደል ማቅረቢያ እንዲጠቀሙ ከተሠሩ ሦስት ኣዳዲስ ፕሮግራሞች ሁለተኛው ነው።
 • ሞክሼ ፊደላትንና እንዚራኖቻቸውን ከማስታወስና በተገኘው መጠቀምንና ግድፈቶችን ይቀንሳል። ሞክሼ ፊደላትን በዓማርኛ ያለመጠቀም ምርጫ ሞክሼዎች የሌላቸውን ሁለተኛ ገበታዎች በማቅረብ ለሚመለከታቸው ሌሎች ቋንቋዎችም ኣውርሷል።
 • ከተለያዩ የቋንቋዎች ገበታዎች የተፈለገውን መርጦ በእዚያ ቋንቋ መጠቀም፤ ለምሳሌ በዓማርኛ ብቻ የሚከትብ የዓማርኛን ገበታ መምረጥ ያስችላል። ግዕዝ ከድምጻዊ ፊደልነቱ ሌላ በኣብሻ ሥርዓት መፈጠር የተነሳ ኣዲስ ኃይል ስለኣገኘ ከዓማርኛ የተረፉት ቁልፎች ለእንግሊዝኛ ተትተዋል። ዓላማውም ኮምፕዩተሩን ለግዕዝ እንጂ ኣንዳንዶቹ እንደሚያደርጉት እንግሊዝኛውን ለግዕዝ ኣይደለም።
 • የኣከታተብ ፍጥነት ማስተካከያ ስለኣለው ኣዳዲስ ጥቅሞች ኣሉት።  ለምሳሌ ያህል በኣብሻ ሥርዓት በተፈጠረው ዘዴ ኣንደኛውን ገበታ በጊዜ ገደብ እንደመሰንጠቅና በመግታት የማይታይ ሁለተኛ ገበታ ተፈጥሯል። ይኸንንም ለመገንዘብ በሁለት ቁልፎች ኣንድና ሁለት መርገጫዎችን በመጠቀም ቀለሞችን መክተብ ይቻላል። ግዕዝኤዲት ግን ብዙ የተሻሻሉ ኣዳዲስ ነገሮች ሲኖሩት በግል ኮምፕዩተሮች ለመጠቀም ነው። ማንኛውም በዩኒኮድ ፊደል የሚጠቀም ፕሮግራም ውስጥ በግዕዝ ሲያሠራ በእንግሊዝኛ በነፃው ወይም በሚሸጠው ግዕዝኤዲት ኣከታተብ (typing) መማርና (ምሳሌ http://www.learntyping.org) ችሎታ ገበታውን ወደ ግዕዝ በመቀየር በግዕዝ መክተብ በግዕዝኤዲት ለመማር ትምህርት ያቀልላል።
 • ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ የተባለው የግዕዝ ዲጂታይዝድ (digitized) ፊደላችን ሁሉንም ያጠቃለለና የተሟላ ከመሆኑም ሌላ በትክክክለኛ ቀለሞች እንድንጠቀም ይራዳል። ምክንያቱም በኣሁኑ ጊዜ ኣንዳንድ የተሳሳቱ ፊደላት መቅረብ ስለጀመሩ ሕዝቡ ከለመዳቸው በኋላ ማሳወቅ ጥቅም ላይኖረው ይችላል። ለምሳሌ ያህል የጥንት ሊቆቻችን ስምንተኛዎቹን እንዚራን ፊደሎች ሲሠሩ የግዕዝ ወይም ራብዕ ቤቶችን መነሻ ኣድርገው ይመስላል። ስለዚህ መነሻስለሆነ ቤቶች ቀለሞች ቀለበቶች እንደ ተስፋ ገብረሥላሴ የ፲፱፻፲፯ .. ቀለሞች የእያንዳንዳቸው ሁለት ብቻ ናቸው። ሦስት ቀለበቶች ያሉት ኃምሱ ስለሆነ የሳልሱም ቅጥያ ቀለበት የሌለው ሦስተኛው እግር ላይ ነው። እንዲሁምእራሱን የቻለ ራብዕ ፊደል እንጂ ታይፕራይተሩ ዓይነትላይ የተቀጠለው ኣይደለም። ግዕዝኤዲት ዩኒኮድ የግዕዝ የመብት፣ የንግድ፣ የተመዝግቧል፣ የብር፣ የሳንቲም፣ የፌዝ፣ የማጥበቂያ፣ የማላልያና ሌሎች ምልክቶችና ኣልቦ ኣኃዝ ኣሉት። 
 • ኩባንያችን ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ካደረገ በኋላ ኣንዳንድ ስህተቶችና ግድፈቶች እንዲስተካከሉ በጽሑፍ ያቀረበውን በግዕዝኤዲትም ተጠቅሞበታል። ለምሳሌ ያህል "" ከምልክት መርገጫ ተነስቶ "E" መርገጫ ላይ የተመደበው "" ሞክሼ ስለሆነ ነው። "" እና "" ወይም "" እና "" ሞክሼዎች ኣይደሉም። "" ስምንተኛው "" ድምጽ ነው።   
 • ሞክሼዎች ሆህያት የሌሉባቸውን “ሃዲስበማለት የሰየምነው ትንሽና ኣዲስ ሁለተኛ ኣማራጭ የፊደል ገበታ የቀረበው በጉዳዩ ተስማማን ማለት ሳይሆን የደራስያንን መብት ላለመንካት ነው በቅርቡ ያንቀሳቀስናቸው። ብዙዎቹ ሞክሼዎች ለክትበት ቅልጥፍና እንዲሰጡ የተመደቡት የእንግሊዝኛ ዋየል መርገጫዎችን በመጠቀም ስለሆነም ከጥቂት ልምምድ በኋላ ግዕዝን ያለምንም የገበታ ሥዕል መክተብ ይቻላል። ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች የሚጠቀሙት በኣንድ 563 ግድም በላይ ቀለሞች ከኣሉት የተሟላ ፊደል ስለሆነ የሃዲስ ኣከታተብ ሲመረጥ የሞክሼዎች መክተቢያዎች የሉም እንጂ ፊደላቱ ተቀነሱ ማለት ኣይደለም። 
 • ግዕዙን በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ መጠቀም ኣያስፈልግም። AእስከZየኣሉት የላቲን የኮምፕዩተር መርገጫዎች እያንዳንዱ የላቲን ሆሄ በኣንድ ቁልፍ እንዲከተብ የተሠሩ እንጂ ኣጠቃቀማቸው ከግዕዝ ኣከታተብ ጋር ግንኙነት የለውም። የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ግዕዝን ከሃያ ስምንት ዓመታት በፊት ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርግ ኢትዮጵያውያን የኣማርኛ ፊደላትን በእንግሊዝኛ የመጻፊያ መሣሪያ (ታይፕራይተር) መክተብ እንዲመች ሲታገሉና ሳይሳካላቸው ከቆዩባቸው የብዙ ዓሥርት ዓመታት ትግል ገላግሏል። ይህ ሊሆን የቻለው ኮምፕዩተሩ ለግዕዝ ኣጠቃቀም እንዲያገለግል ከኣዳዲስ ገበታዎች ጭምር ስለፈጠረ እንጂ የእንግሊዝኛ ፊደል ለግዕዝ መክተቢያ እንዲያገለግል ኣይደለም። ተጨማሪ ምክንያትም ኣሁን በኣብሻ ዘዴ የግዕዝን ቀለሞች እንደ እንግሊዝኛው በኣንድና ሁለት ቁልፎች መክተብ ስለተፈጠረ ነው።
 • በኣብሻ ሥርዓት ከቀረቡት ኣንዱ ጥሩ የፎነቲክ ዘዴ ስለሆነ የግዕዝና እንግሊዝኛ ድምጻዊ ቀለሞች የሚጋሯቸው ወደ 18 የቀረቡ ቍልፎች ኣቀማመጦችና ኣከታተቦች የተቀራረቡ ናቸው።
 • ኣንድ ጽሑፍ  ሰባት ለመክተብ የሚያስቸግሩ 24 ቀለሞች ያሉት የዓማርኛ ቃላትን (ሐመር፣ ኋይት ሃውስ፣ ሦስት፣ ቋንቋ፣ ትዕግሥት እና ጨካኝ) ሁለት የዓማርኛ ሶፍትዌሮች 51 እና 55 ቁልፎች ሲጽፉ ሦስተኛው ኣንዱን ቃል በጠመዝማዛና ረዥም መንገድ እንጂ በመደበኛው ኣካሄድ መጻፍ እንዳልተቻለ ኣቅርቧል። እነዚህኑ ቃላት የኣብሻ ሥርዓት የሚያስከትበው 32 ወይም 34 ቁልፎች ስለሆነ ድካምና ጊዜ ከመቀነስ ሌላ ሕዝቡ በቀላሉ በሚገባው መንገድ እንዲጠቀምበት የተሠራ ነው። (የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር በ፲፱፻፹ .. ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ያደረገበትን ሲያቀርብ እያንዳንዱ ቀለም የተከተበው በሁለት መርገጫዎች ነበር። ግዕዝን በእንግሊዝኛ ፊደል እስፔሊንግ ዘዴ ለመጻፍ የተጀመረው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር 37 የግዕዝ ግዕዝ ቤት ቀለሞች የመደበውን መርገጫዎች ገልባጮች 26 የላቲን ፊደላት በመመደብ በጀመሩት ግልበጣ ነው።ፊደል መጻፍ ያለበት A እስከ Z ባሉት መርገጫዎች ብቻ መሆን ያለበት የሚመስላቸውና ኣለማወቃወቃቸውን የማያውቁ ኣሉ።
 • የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርግ የእንግሊዝኛውንና የግዕዝ ፊደላቱን በተመጣጠን መጠን እንዲቀርቡ ሁለቱንም በኣንድነት በመሥራት ኮምፕዩተሩ ላይ ያሉትን የእንግሊዝኛ ምልክቶችንም ለግዕዝ ሲጠቀምባቸው ቆይቷል። በኣብሻ ዘዴም እነዚህን 32 ምልክቶች በየሁለት መርገጫዎች ብቻ መክተብ ስለሚቻል በእነሱ ለመጠቀም ወደ እንግሊዝኛ ገበታ መቀ'የር ምርጫ እንጂ ግዴታ ኣይደለም። እንዲህም ሆኖ ከግዕዝ ወደ እንግሊዝኛ ለመዞር ከኣሉት ዘዴዎች ኣንዱ የቁጥጥርና ኣማራጭ (Ctrl-Alt) ቁልፎችን መጫን ነው።
 • ጊዜና ጣቶቻችንን ከማትረፍ ሌላ ከኣሁን ወዲያ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስትና ከእዚያም በላይ መርገጫዎች በመጠቀም መክተብ ኣያስፈልግም። ምክንያቱም ብዛታቸው 563 ግድም በላይ የሆኑትን የግዕዝ ቀለሞች ልክ እንደ እንግሊዝኛው ቀለሞች የፊደል ገበታ ኣጠቃቀም (2 x 47+47=141 መርገጫዎች) እያንዳንዳቸውን በየኣንድ መርገጫዎች ከመክተብ የተረፉትን በየሁለት መርገጫዎች ብቻ መጠቀም የሚያስችል ኣዲስ ኣብሻ (ABSHA) የሚባል ዘዴ ስለፈጠርን ነው። ስለዚህ ወደ እንግሊዝኛው የኮምፕዩተር መርገጫዎች ቀልጣፋ ኣጠቃቀም በቀረበ ፈጠራ 564 ግድም የግዕዝ ቀለሞች የሚከተቡት 1081 ወይም (2 x 517+47) መርገጫዎች ወይም ቁልፎች ነው።  እዚህ ላይ ኣንድ ተጨማሪ መርገጫ እንኳን መጨመር ለሚሊዮን ተጠቃሚዎች ሚሊዮን ረገጣዎችን መጨመር ነው።  ከእዚህም ሌላ የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያድርግና በኣብሻ ሥርዓት ከፈጠረው ውጪ የኣከታተብን ሕግ በመከተል ግዕዝን ያስከተበ ዘዴ የለም።
 • የዓማርኛ ቀለሞች ብዛት ከሁሉም የግዕዝ ቀለሞች ጋር ሲወዳደሩ ሁለት ሦስተኛ ያህል ቢገመቱም በኣሁኑ ጊዜ ሌሎች ዓማርኛውን የሚከትቡት ለኣንዳንዶቹ ቃላት ኣራትና ከእዚያም በላይ ቁልፎችን በመጠቀም ነው።  የብዙዎቹ ሌሎች ቋንቋዎች ቀለሞች ከዓማርኛው የበዙ ስለሆኑ ኣንዳንዶቹን ለመክተብ እስከ ሰባት ቁልፎችን መጠቀም ሳያስፈልግ ኣይቀርም። ለምሳሌ ያህል በእንግሊዝኛ እስፔሊንግ እንዲከተብ ከተፈለገ 8 መርገጫዎች (CCCie) ለመክተብ የታጨ የጉሙዝ ቀለም ስለኣለ ችግር ውስጥ እንዳንገባ ግዕዝኤዲት ገላግሎናል። በኣብሻ ኣከታተብ ግን ሁሉም የግዕዝ ቀለሞች የሚከተቡት በኣንድና ሁለት መርገጫዎች ብቻ ስለሆነ እኩልነት እንጂ ማዳላትና ግፊያ የለም። ስለዚህ ጥቂት የቁልፍ መርገጫዎችን በመጠቀም በረቀቁና ፈጣን ዘዴዎች ድረገጾችንም በቀላሉ መጎብኘትና መሥራት ይቻላል።

English እንግሊዝኛ

GeezEdit Features:

 • Typing is very simple using one keystroke for the default and the rest with a maximum of two keystrokes each, just like typing in English. 
 • Typing is based on science. For instance, Amharic uses the sixth order characters the most and each is typed with a keystroke. 
 • Each computer key has its own Ethiopic name, just like the English key name. 
 • Key assignment is based on potential number of users. 
 • It was invented by people with over 25 years of experience with Geez on computers. 
 • It is based on a new, simple and fast computer technology protected by pending patents and U.S. Patent 9,000,957..
 • It is for use in any Unicode compliant application with conventional typing methods where default characters are typed with one keystroke each just like English. Controlled timeouts allow the typing of two default characters with two keystrokes while any glyph can be doubled with two keystrokes or typed with a maximum of two keystrokes. Thus, there is no need to settle for typing tools that do not type all the characters. There is also no need to toggle through three characters, or type by inserting spaces and leave them within words or remove them with delete keys after using arrows or type the Ethiopic in English spelling and transliterate on pressing the space bar or use the mouse to select words from a list, or mouse click on characters to type them.
 • GeezEdit is the second of three applications with the same novel rendering technology for Windows and Mac computers.
 • It eliminates the need to remember redundant Ethiopic character series (ሞክሼ) and their random usage. 
 • It expanded the option to avoid redundant Amharic characters to other relevant languages. 
 • The typing of different language glyphs is optionally accessed by a drop-down menu so that an Amharic typist would have only the Amharic character sets and keyboards. Keys not used by the Amharic (or any of the other languages) revert to English.
 • The general layout is similar to ModEth, EthioWord and other applications by ECS known to thousands of users. 
 • The typing speed is adjustable to control the expanded keyboards and typing is conventional just like English eliminating the use of unconventional keys such as space bar, mouse, arrows, delete keys, etc. for typing Geez glyphs. 
 • There is no need to spell Ethiopic in English to render it on computers. This is because Ethiopic is a syllabic alphabet; not words. The current methods are based on futile political decisions besieged with numerous issues ignored because there were no solutions so far. Our scientific invention expanded the keyboard also eliminating the limitations of the English alphabet that invites spelling errors, the type that is alien to Ethiopic. ABSHA system is simple and all the user has to remember is the usage of the of vowels and keys used as vowels as Ethiopic orders with the optional use of the keyboard pictures that appear on the screen showing the 37 Ethiopic primary characters that have been assigned to the 37 computer keys. 
 • In one observation seven difficult Amharic words (ሐመር, ኋይት ሃውስ, ሦስት, ቋንቋ, ትዕግሥት and ጨካኝ) with 24 glyphs were typed with an average of 53 keystrokes by two software while the third had issues typing one word. GeezEdit types these same 24 glyphs with 32 to 34 keystrokes which drastically simplifies the typing process and saves time also because its presentation is easily understandable by Ethiopic users.
 • Spare your time and fingers and from now on there is no need to use three or more keystrokes to type any Ethiopic glyph. For instance, "እእ" is typed with two keystrokes of the "" key; not with four or more keystrokes. ABSHA is close to typing the English on computers with one keystroke each for the default and two keystrokes for the capitals and symbols in the shifted positions. The English glyphs on the computer keys are typed with 141 (2x47+47) keystrokes. With this novel technology the 564 Ethiopic glyphs are typed with 1081 (2x517+47) keystrokes. Using more than 1081 keystrokes is not an advantage. Even one more keystroke is a large number for the millions of users.  
 • Amharic comprises about two thirds of the Ethiopic glyphs and is the most important character set currently typed with many keystrokes by others. We hear less about the other minority language glyphs most likely because of the need to use up to 8 keystrokes and the potential for resentment. Ethiopic got into all these problems because Ethiopia did not have a patent system at the time Ethiopic was computerized and each character was rendered with two keystrokes. There is now a patent and pending patent. ABSHA eliminates these through fairness and equality of keystrokes as each Ethiopic glyph is typed with one or two keystrokes. Type less, do your job smarter and surf the web faster in Ethiopic. 
   

GeezEdit 2.0 Screenshots ሥዕሎች:

GeezEdit Advertisement የግዕዝኤዲት ማስታወቂ